International Ethiopian Women's Organization (IEWO

Ethiopian Unity Peoples Voice Congress Party
Home
International Ethiopian Women's Organization (IEWO)
About Us: IEWO's Objectives and Mission
IEWO Radio and Audio Files
Boycott
Articles and Papers
Articles
Special Events Audio Files
IEWO's Leadership Group
Press Release and News
Ethiopian Unity Peoples Voice Congress Party
Poems and Letters [letter from South Africa]
Discussions, & Comments
Members Registration Page
Health Matters and Wellness
Contact Us
Recent and Upcoming Events
March 8 Celebration and The Frist Congress of IEWO
Links and Resources

የኢትዮጵያ አንድነት የሕዝብ ድምጽ ምክር ቤት ፓርቲ ።

P.O. Box 860374 Plano, Texas 75086E-mail eupvc@yahoo.com

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

አለም አቀፍ መግለጫ ይድረስ ለመላው የኢትዮጵያ ባለቤት ለሆነው ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ። የኢትዮጵያ ሴቶች ለሰላም እና ለዴሞክራሲ/የኢትዮጵያ አንደንት የሴቶች ድምች ምክር ቤት በጣምራ፡የኢትዮጵያ አንድነት የሕዝብ ድምጽ ምክር ቤት በሚል በአንድ መልኩ መደራጅቱን እንገልጻለን።

 

August 1, 2008 ዳላስ ቴክሳስ።

 

በአውሮፓውያን አቆጣጠር ሜይ 15 ቀን 2008 ሁልት ድርጅቶቻችንን ማለትም የኢትዮጵያ ሴቶች ለሰላም እና ለዴሞክራሲ/የኢትዮጵያ አንድነት የሴቶች ድምጽ ምክር ቤት ፓለቲካል ፓርቲን በነጮች አቆጣጠር በ1986 ተመዝግቦ ከተቆዋቁዋመበት ጊዜ ጀምሮ ብዙ የፓላቲካ ስራዎችን ፡ የተለያዩ በውጪም በአገር ቤትም የሚገኙ ለአገር አንድነት የቆሙትን ድርጅቶች በመርዳት ከጎናቸው በመቆም፡ ተወካይ በውጭው አለም የሌላቸውንም ከአገር ቤት በማምጣት ነጻ መድርክ በመፍጠር ፡ ከሕዝቡ ጋር በስብሰባ መልክ በመገናኘት ስለ ፓሪትያቸው አላማ እና አቅዋም እንዲያስረዱ፡ እርዳታም እንድያገኙ በማድርገ ብዙ አስተዋጽዖ አድርገናል። ከባድ ሃላፊነት በመሸከም ከማንም ገንዘብ ሳንጠይቅ በራሳችን ገንዘብ እና ጊዜ በመውሰድ ያልተቁዋረጠ ትልቅ ሃላፊነት የኢትዮጵያን ስዴተኞች ተቀባይነት እንዲያገኙ ብሎም በገንዘብ ሳይቀር፡ ስናስተናገድ እና ጉዳያቸውን ስናጽፈጽም ስንሰራ ኖረናል ይሄውም በቅርብ በጣሊያን ማልታ ለነበረው ችግር መፍትሄውን ያለማንም እርዳታ ብቻችንን በመወጣት ብሎም በሊቢያ ስላሉት፡ በጅቡቲ፡ በሱዳን፡ በኬኒያ፡ በዩጋንዳ እና በአረብ አገር ስለነበሩት ስላሉትም በባርነት ተይዘው ስለሚሰቃዩት ኢትዮጵያውያን ሲቶች እና ጥቂት ወንዶች ለአለም ለሚገባው ሁሉ ያስታወቅነው እና ጉዳዩን በስራ ላይ አውለናል። የኢትዮጵያን ባሕር ሃይል ጀግኖችንም የጨምራል ያደረግነው ተግባር። HR-bill በአሜሪካን ምክር ቤት ስለ ቀረበው ሃሳቡን ካለን ልምድ በማፍለቅ ነድፈን ስራላይ እንዲውል ያቀረብነው እኛው ሴቶቹ ነን። ይሄንን ስንል የሰራንውን ለማዳነቅ ሳይሆን ስራ ስለ አገራችን ስንሰራ የኖረን ብዙም ስራዎችን መስራት የምንችል እና በእውቀታችንም አገራችንን እና ሕዝባችንን የምናኮራ የኢትዮጵያ ዜጎች መሆናችንን ለመግለጽ ብቻ ነው። ሕዝብ በኛ ስራ ሊተማመን የሚችለው የሰራንውን ሲያውቅ ብቻ ነው። የመጀመሪያ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ተቀዋሚ ድርጅት መስርተን ለሴቱም ለአገራችንም ክብር ስንታገል መኖራችን ለኛ ብቻ ሳይሆን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያኮራ ነው። በኢትዮጵያ የፓለቲካ ፓርቲ ታሪክ ውስጥ አንዱም ፓርቲ ባጠቃላይ የኢትዮጵያን ሴቶች ስለ አገራቸው እነሱንም ይመለከታል ፡ መፍትሄም ለማምጣት የለውጡ ጥንስስ እና ጠማቂም ሊሆኑ ይገባል ከወንዱ እኩል ኢትዮጵያ ለነሱም አገራቸአው ንች እስቲ ብሎ በሃላፊነት ፡ በወሳኝነት፡ በስልጣን አመራር ወንበር ላይ አንድም ሴት ያስቀመጠ ድርጅት ፈጽሞ አልነበረም አሁንም አንዲት ሴት በራስዋ አይምሮ የምትመራ ተቀብሎ በፓርቲው ያስገባም የለም ለይስሙላ ተጠርተው ሴት አለችበት ለማሰኘት ሴት ካስገቡት በስተቀር። አሁንም ያው ነው ነይ እዚህ ፓለቲካ ፓርቲያችን ውስጥ ግቢና አገልግይ፡ በሚል ከመንገድ ጎትቶ አሳምኖ የምንልሽን ስሪ ፕሬዘደንት እናደርግሻለን ማለት፡ የሴትዋን እኩልነት ጠበቀ ማለት አይደልም። ስለዚህ ላለፈው 22 አመታት ቀድም ብለን መብታችን የአገር ባለቤትነታችን እንዳልተከበረ የተረዳንው ሲቶች፡ ግንባራችንን ሰጥተን ሴቶች በእየድርጅቱ እንደ እየችሎታቸው በየፓለቲካው ፓሪቲ መግባት  እንዳለባቸው በግንባር ጪምር እየተገኘን ታግለናል። በምንኖርበት አካባቢ ሁሉ ሴቶች በመረዳጃ ማሕበራት እና በሃይማኖት ተቅዋማት ጭምር ግልጽ የስራ እና የሃላፊነት የወሳኝነት ስልጣን በችሎታቸው ደረጃ እንዶኖራቸው አድርገናል።  በያለንበት ሰላማዊ ሰልፍ ለማዘጋጀት ወንዱ ባላሰበ ጊዜ እኛ ሴቶቹ የኢትዮጵያ ሲቶች ለሰላም እና ለዴሞክራሲ ሰላማዊ ሰልፍ በመጥራት ሕዝቡን በየከተማው በመቀስቀስ፡ የአሜራክንን ጋዜጠኞች በማሳመን በየጊዜው በራሳችን በመነሳሳት ብዙ ፓርቲዎችንም አሳትፈናል። ላለፈው 25 አመት የሚታወቀውን የኢትዮጵያ እስፓርት ፈደሬሽን በሰሜን አሜሪካ የሕዝብ እንዶሆን ሃሳቡን ጥንስሰን በደረግነው ትግል ሕዝባዊ ያደርገንውም እኛው ሴቶቹ ነውን። ሴቶች ወጣቱን በፈደሬሽኑ በአል ላይ ባሕሉን እና ታሪኩን ተረካቢ እንድሁም ፈደሬሽኑን ተረካቢ እንዲሆን፡ ለሴቶች ፕሮግራም ነድፈን በማቅረብ በመታገል ብዙ መከራን ብንቀበልም፡ ባአለፈ የፈደሬሽኑ 25 በአል ወጣቱን ይዘው የቀረቡት ሴቶች የእኛ መታገል ውጤት ናቸው። የፈደሬሽኑም የሕዝባዊ ድርጅትነት መስራች ነኝ። በጥቅሉ ምን አስተዋጽዖ አድርጋችሁዋል ለሚለው ጥያቄ ባጭሩ ገልጸን ልንጨርሰው የሚቻል ካለመሆኑም በላይ፡ አላማችን ስለሰራነው ለማውራት ሳይሆን ስለ አገሩ ተከታትሉ ስለማያውቀው እና አዲስ ሰሚ ለሆነው ብሎም ለወጣቱ በብዙ ትግል ተራራ የወጣን የወረድን መሆናችንን እና ስለ አገር አንድነት የቆሙትን እና አንድነትንም በማፍረስ እራሳቸውን ቁንኞ ለማድረግ የሚርዋሩዋጡትን ግልሰቦች አጥብቀን እንደምናውቅ እንዲታወቅልን ጭምር ነው ይሄንን ያህል ያተትነው። ሴቶች ምንም አይሰሩም መላካቸውን ብቻ ማሳመር ነው ወሬ ነው ስለ ቁሳቁስ እና ገንዘብ ያለውን እየፈለጉ የሩጡ እንጂ የሚለውን የጥምር በጥቂቶች የተሰጠንን ጸባይ እና አነጋገር እውን አለመሆኑን በስራ ስለሳየን ፡ የለወጥናቸውም እንዳሉ አይተናል። ሆኖም ገና ብዙም መንገድ መጉዋዝ እንዳለብንም እናምናለን ያለሴቶች አገር ሰላም እና አንድ ልትሆን እንደማትችል። ባጭሩ የመጀመሪያ የኢትዮጵያ ሴቶች በተቃዋሚ መልክ ዴሞክራሲን ለአገራችን እና ለሕዝቡ ለማከናነብ ፓርቲ በስማችን የኢትዮጵያ ሴቶች ለሰላም እና ለዴሞክራሲ/የኢትዮጵያ አንድነት የሴቶች ድምጽ ምክር ቤት ፓርቲን  መስርተን፡ በተለያየ የፓለቲካ ዘርፎች የውጭ ጉዳዩንም ጭምር በማጣመር ስንታገል የኖርን እና እየሰራንም ያለን የመጀመሪያ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ነን። ከወንዶቹም ያላነሰ ችሎታም እውቀትም ያለን ሴቶች እንዳለንም በተግባር አስመስክረናል። ብትግሉ ውስጥ በጦርም ሜዳ ያገለገሉ እህቶቻችን እንደነበሩ እና በሕይወትም ተርፈው ያሉም እንዳሉ እናውቃለን። ሆኖም እነሱ በፈጠሩት ሆነ ብለው አምነውበት ሳይሆን ጥቂት ወንዶች ከፈረንጆች በተዋሱት መጸሃፍ አማካኝነት በፈጠሩት የለውጥ ትግል መጠቀሚያ ይሆኑ እና ከዛም ፓርቲዎች አንድም ቦታ በሃላፊነት በወሳኝነት ሳያስቀምጥዋቸው በማየታችን በመቆጨት የተነሳን ነን። በታገሉት እቶቻችን እንኮራለን በተግባር ያሳዩትም የኢትዮጵያ ሴቶች ታጋይ እና ቆራጥ የስሜት ተገዢዎች እንዳልሆንን ምስክራችን ሆኖዋል።

 

ባጭሩ አንጋፋ ፓርቲዎች ጎን ተሰልፈን ከ2005 ምርጫ በሁዋላ የላላውን ትግል በማጠናከር አገራችንን መልሰን ለመገንባት ከመቼውም የበለጠ ታጥቀን ከዚህ በመቀጠል፡ በምናቀርባቸው ምክኒያቶች ተነሳስተናል።

 

 

ኢትዮጵያን ከወደቀችበት የትግሬ ነጻ አውጭ እጅ ነጻ ለማውጣት ብሎም በተዘዋዋሪ መንገድ እየወረስዋት ካሉት አረቦች ለማዳን፡   ስንል ሁሉቱን ድርጅት በአንድ ስም አዋህደን ሰፋ ባለመልኩ ወንድሞቻችንንም በመጨመር የአንድነት ክንድ የኢትዮጵያ አንድነት የሕዝብ ድምጽ ምክር ቤት ፓርቲ በሚል ሰይመንዋል። የታወቀውን የእርግብ አርማችንንም በመቀየር፡ ሴቱንም ወንዱንም የሚወክል ከኢትዮጵያ ታሪክ የወረስነውን የወንድ አንበሳው እንዳለ ሆኖ ፡ በታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያን ጀግኖች ሴቶችን የምታንጸባርቅም አንበሳ ባንጻሩ አስቀምጠናል። የሄም ለዘላለም ወንድሞቻችንንም እኛንም ሲቶቹን የሚወክል የአንበሳነት አርማ ነው። ክብራችንን ማንሳቱ ከዚህ ይጀምራል።

 

ስለ ድርጅቶቹ በአንድ መልክ መቁዋጨት፡ ከአንድ ወር በፊት፡ በአለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሲቶች ድርጅት ሬዲዮ እና ፓልቶክ  ላይ እህቶቻችን በሰጡን የእህትነት እና የአክብሮት መድረክ ላይ በመገኘት፡ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት የሕዝብ ድምጽ ምክር ቤት ፓርቲ በሰፊው መዘርጋቱን እና የተነሳንበትን አላማ እና ምንስ ልንሰራ እንደሆነ እቅዳችን ለተሳታፊው ወገን መግለጻችን የማይዘነጋ እና ብዙውን ሕዝብ እያነጋገረ ያለ ተሰፋ ነው። ሕዝቡም ደስታውን እና ምክሩን ጭምር ለግሶናል። ትልቅ ሃላፊነትም አስረክቦናል ይሄንን ስንል ወንድሞቻችን ጪምር ማለት ነው። እኛም ከአለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት ጋር በአንድነት እንደምንሰራ እና አንድነታችንንም ማነው እንደማያፈርሰው ግልጽ አድርገናል በማያወላውል መንገድ።

 

 

ለምን የኢትዮጵያ አንድነት የሕዝብ ድምጽ ምክር ቤት ፓርቲ ተመሰረተ?

 

1ኛ። በትግሬ ነጻ አውጪ እና በአረቦች እጅ የወደቀችውን ኢትዮጵያን እና     ሕዝብዋን ነጻ ለማውጣት።

 

2ኛ፡ የትግሬ ነጻ አውጪ የኢትዮጵያን ዳርድንበር ለሱዳን በማስረከቡ።

 

3ኛ፡ ሕዝቡን ለሱዳን እስር ቤት በማስረከቡ።

 

4ኛ፡ የኢትዮጵያን ሕዝብ የትግሬ ነጻ አውጪ በሜዳ ሆኖ ከሊቢያ፡ ከኢራክ፡ ከሳውዲ አረቢያ፡ ከየመን እና ከሱዳን ጋር ያደረጋቸውን ውል በሙሉ፡ በጉልበቱ በሊቢያ ወታደሮች እየተመራ በደብረዘይት ወደ አዲስ አበባ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ፡  የሊቢያው መሪ ጋዳፊ እንኩዋን ኢትዮጵያን ወደ አረብነት መለሳችሁዋት ቃል በገባችሁት መሰረት ከአርቦች ወንድሞቻችሁ ጎን እንደገና በመቆማችሁ መመስገን አለባችሁ ኮራንባችሁ፡ በሚል ለመለስ እና ለጥቂት የትግራይ ተወላጆች በትግሬ ነጻ አውጪ ስም ያስተላለፈውን መልእክቱን በማስተባበል አገር እንደማይስገነጥል ለአረቦችም አገር እንደማይሰጥ እግራቸው ኢትዮጵያን እንደማረግጥ ነብር መለስ የተናገርው። ሆኖም በሚስጥር የጀመረው አገር መሸጥ በካራቆሬ የጀመረው ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ እየገሰገሰ ነው። ሆኖም ስለአገራችን አተኩረን ሳንተኛ የምንታገልው የምንከታተለው ካራቆሪን ለአረቦች መሸጥ እና ሚሊየነር ነው እየተባለ በሃሰት የኢትዮጵያን ሕዝብ ለማታለል በሚወራለት ግማሽ ኢትዮጵያዊ ግማሽ የመን የተዘረጋው የአረቦች መንገድ በቦሌ ቀይ ምንጣፍ እየተነጠፈላቸው ለኢንቬስትመንት በሚል እየገቡ ነው። የወርቁን ማእድን ብሎም የእብነ በረዱን ወርሰዋል በዚሁ በግማሽ ኢትዮጵያዊው አማካኝነት አገር እየተሸጠች ስለሆነ።

 

5ኛ፡ መለሰ ፡ ትግሬን መለሶ ለማቁዋቁዋም ሻቢያ ደበደበን በሚል ስም ውጪ ያለንውን አታሎን፡በዛ ሰበብ በመሃላችን  በትግርኛ ተናጋሪዎች አማካኝነት ወኪሎቹን አስገብቶ 82 ሰዎች ኢትዮጵያ ሄደው ባድማ ደርሰው ሕጻኑን በተለይ የአማራውን እና የኦሮሞውን ልጅ ከየገጠሩ ታድሎ ለጦርነት እዳ አድርገው ሲመለሱ፡ ይዘው የመጡት ቢኖር ፡ የክልል ኢንቪስትመንት የገበያ ማስታዋወቂያ በራሪ ወረቀቶች ነበር። በዛው መሰረት ትግሬኛ ተናጋሪው የወያኔን መልእክት ማለትም ሕዝብ መሃል ገብቶ ለአገራችን አንድነት የምንታገለውን እንዲያዳክቡ በየከተው ተደረጉ። ሆኖም እንዳሰቡት ስራ ላይ አልዋለም። ቀጥለው በውጭ የሚደረገውን ትግል ለማዳካም እንዳልቻለ ሲያውቁ፡ በገንዘብ መረብ ገብጋቦች እራስ ወዳዶች ከገንዘብ ሌላ ምንም ሕሌናቸው ስለ አገራቸው የማያስብ እየፈለጉ፡  በማጥመድ ትግሉን ለማደንገዝ እና ለመግደል የጀመረውን ከኢትዮጵያ ጨርሶ ወደ አሜሪካን ገብቶ በስራ ላይ ህልሙን ወያኔ በበለጠ እያጠናከረ መሆኑን ስለደረስንበት።

 

6ኛ፡ ወያኔም የገዛቸው የወንድ ቅምጦች፡ በተለያየ መልኩ ወደፊት በምንገልጽው በተዘረጋላቸው ሕዝብን በመከፋፈል እና ትግል በማፍዘዢያ ዝግጅት እየሰሩ መሆናቸውን ስለደረስንባቸው። እነዚህም ግለሰቦች ከሩቅ የመጡ ሳይሆኑ በየከተማው አጠገባችን ወዳጅ ፡ ማህበርተኛ ብሎም ነጋዴ ነን የሚሉ ጭምር ይገኝባቸዋል።

 

የማንቀበላቸው፡  

ቀደም ሲል መለስ እና ግብረ አበሮቹ በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም ያደረጉትን ማንኛውንም ውል እና ፊርማ የኢትዮጵያን ሴቶች በአገራችን ጉዳይ ላይ ያካተተ ስላልሆነ ተቀባይነት በኛ በኩል እንደሌለውን እና እንዳልተቀበልነው የጸና አላማ   አሁንም ወደፊትም የማይላላ፡ የማይሰበር፡ የማይልፈሰፈስ አቁዋማችን እንደጸና እና የትግሬ ነጻ አውጪን በመለማመጥ እሹሩሩ በማለት እንደማናምን ግልጽ እንድሆን እናስታውቃለን። ይህንንም ስንል ማንም ተልካሻ ፡ እራስ ወዳድ፡ አድር ባይ፡ ለራሱ የማይቆም፡  አገሩን እና ወገኑን ለኪሱ አሳልፎ የሰጠ ኢትዮጵያ የማትኮራበት ከንቱ ወንድ፡ ሊገረስሰው ባልቻለው እና  በማይችለውም በኢትዮጵያዊነት ኩራታችን መሆኑን ስናስቀምጥ ከወረስነው የኢትዮጵያዊነት ኩራት ጋር ነው።

 

ኢንቬስትመንት ኢትዮጵያ ውስጥ እንቀበላለን እኛም ሕላማችን ነው። ነገር ግን ወያኔ ብቻውን በሚውስነው ሳይሆን፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ አገሪቱን ሲረከብ ያኔ ኢንቬስትመንት በየት አካባቢ እና ምንላይ ቬስትመንት ማድረግ ማን እንደሚችል ለአለም እገበያላይ ባለቤቱ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ በህግ የሚመራ ምክር ቤት ሲኖረው የሚያደርገው ጉዳይ ይሆናል። አሁን አንድ ሰው መለስ ዜናዊ ብቻ ነው የኢንቬስትመንቱም የሁሉም ውሳኝ ፡ ስለዚህ የሚፈራረመው ሁሉ አይጸድቅም ሊጸድቅም አይገባም። እስካሁንም ኢንቬስት ላደረጉት እና ለማድረግም እያኮበኮቡ ላሉት ውላቸው ቦታ እንደሌለው እና ሊኖረውም እንደማይችል እንዲረዱት የገባል  በበለጠ።

 

 

በሚቀጥለው መግለጫችን ስለምንሰራው እቅድ እና እየሰራን ስላለንው በተመለከተ ብቻ ባጭሩ እናቀርባለን።

 

ኢትዮጵያ ለዘላለም በሴቶች እና በወንዶች አንበሶች ልጆችዋ ታሪክዋን እቦታው መለሳ እንደቀድሞው ክብርዋን አስጠብቃ ተፈርታ እና ተከብራ ለዘላለም ትኖራልች። አረቦች እና ሱዳኖች የኢትዮጵያ ባለቤት አይሆኑም! ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ሕዝብ ስለሆነ ሕዝብን የአገሩ ባለቤት እናደርገዋልን!

ድሎ የኢትዮጵያ ሕዝብ እና አገራችንን በገንዝብ በግል ድሎት ብልጫ አሳልፈን የማንሰጥ ቆራጥ ኢትዮጵያውያን አንበሶች ብቻ ይሆናል! አሸናፊ ውነተኛ ነው እውነት አንዲት ኢትዮጵያ ነች!

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Enter content here

Enter content here

Enter content here

Enter supporting content here

Copyright 2004 Network of Ethiopian Women (NEW) International