International Ethiopian Women's Organization (IEWO

Boycott
Home
International Ethiopian Women's Organization (IEWO)
About Us: IEWO's Objectives and Mission
IEWO Radio and Audio Files
Boycott
Articles and Papers
Articles
Special Events Audio Files
IEWO's Leadership Group
Press Release and News
Ethiopian Unity Peoples Voice Congress Party
Poems and Letters [letter from South Africa]
Discussions, & Comments
Members Registration Page
Health Matters and Wellness
Contact Us
Recent and Upcoming Events
March 8 Celebration and The Frist Congress of IEWO
Links and Resources

 

በዲያስፖራ (Diaspora) በምንኖር ኢትዮጵያውያ በተለይም በዓለም አቀፍ

የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት አነሳሽነት የተጀመረው (ቦይኮት ወያኔ) እንቅስቃሴ፤

ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ አገሮች (በተለይም ወደ ሰሜን አሜሪካና አውሮፓ) ለሽያጭ የሚመጣ እንጀራ ማንም እንዳይገዛው ለማድረግ ካለፉት ሁላት ወራቶች ጀምሮ በተለያዩ ሚዲያዎች ሲነገር ቆይቷል::

ቦይኮቱ ያስፈለገበት ዋናው ምክንያት በሀገራችን ብዙ ህዝብ ምግብ በማጣት በርሃብ እየሞተ ባለበት በአሁኑ ወቅት ጤፍ እንጀራ ወይንም ማንኛውንም ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ የሚላኩ የምግብ ሸቀጦችን መግዛት ማለት ከራብተኛው አፍ ነጥቆ እንደመብላት ስለሚቆጠር ኢትዮጵያውያን በዚህ ተግባር ላይ እንዳይተባበሩ ለማሳሰብና ለማንቃትም ጭምር ነው:: በውጭ አገሮች የምንኖረው ኢተዮጵያውያን ብዙ የምግብ አማራጮች ስላሉን ከኢትዮጵያ የሚመጣ እንጀራ ቦይኮት ብናደርግ ምንም የሚጎዳን ነገር የለም:: እንዲያውም በተቃራኒው የወያኔን ሸቀጦች ቦይኮት በማድረጋችን ለወገኖቻችን ጥሩ ነገር እያደረግን እንደሆነ ልንዘነጋ አይገባም::

ወያኔ የምግብ ሸቀጦችን ከተራቡ ሀጻናት አፍ እየቀማ በመሸጥ በሚያገኘው ገንዘብ መልሶ ያንኑ ጭቁን ህብ መረሸኛ ሰለሚያደርገውና ለመጨቆኛ ተቋሞቹ ማጠናከሪያ ሰለሚያውለው፡ በወያኔ የሚላከውን እንጀራ በመግዛት ወያኔ በሚፈፅመው ወንጀል በቀጥታም ሆነ በተዛዋሪ ተጠያቂ ሊያደርገን ይችላል::

በዚህ በክፉ ወቅት እንጀራ ወይንም ማንኛውንም የምግብ ሸቀጥ ወደ ውጭ አገሮች እያወጣ በመሸጥ አረመኔው የወያኔ አገዛዝ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፎችን ለመምታት የሚጠቀምበት መሳሪያ ነው:: በአንድ በኩል እንጀራ ወደ ውጭ አገሮች እየላከ በመሸጥ የውጭ ምንዛሬ ለማገኘት ሲያስችለው (ከድሃው ገበሬ በርካሽ ዋጋ በመግዛትና በጣም በውድ ዋጋ በዶላር ወይንም በኢሮ በመሸጥ) ሁለተኛው ሊያስመዘግበው የሚፈልገው የፖለቲካ ጥቅምም አለው:: ይኸውም ወያኔዎች በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ርሃብ የለም፤ የተጋነነ የጠላት ወሬ ነው ብለው ስለካዱ አህል ሞልቶ ተርፎ ወደ ውጭ አገሮች መሸጥ እንደሚቻል ለዓለም ለማሳየት ነው:: ሌላው ከዚሁ ጋራ የተያያዘው ጉዳይ ከኢትዮጵያ የሚመጣውን እንጀራ የሚሸጡትም ሆነ የሚገዙት(የሚቀበሉት ነጋደዎች) ከወያኔ ጋራ ግንኙነት የሌላቸውና ነፃ ወይንም ገለልተኛ ነጋደዎች መስለው እንዲታዩ ለማድረግ ነው:: ነገር ግን ሃቁ በዛሬዋ ኢትዮጵያ ውስጥ እንጀራ አሁን እየተሸጠ ባለበት ደረጃ ይቅርና ማንኛውንም ጥቃቅን የንግድ ሥራ የሚቆጣጠረው ወያኔ ብቻ እንደሆነ ዓለም ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ሀቅ ነው:: ነፃ ነጋደዎችንማ ወያኔ ከኢኮኖሚ ጫዎታ ውጭ ካደረጋቸው ብዙ ዓመታት ተቆጥረዋል::

ቦይኮት ቅኝ ገዥዎችንም ሆነ አምባገነኖችንና እንደዚሁም ዘረኝነትን ለመዋጋት ብዙ አገሮች ተጠቅመውበታል:: ለምሳሌ በአሜሪካ ውስጥ ቦይኮት የሚለው ቃል ገና ከጥቅም ላይ ከመዋሉ በፊት ከባርነት ነፃ ለመውጣት በባሪያ ጉልበት የሚመረት የእርሻ ምርት ማንም ገዝቶ እንዳይጠቀምበት ከባርነት ነፃ የነበሩ ጥቁሮች ቅስቀሳ ያደርጉ እንደ ነበረ ከታሪክ ለመረዳት ይቻላል:: እንደዚሁም በአሜሪካ የእንግሊዝ ቅኝ ገዝዎች የእንግሊዝ መንግሥት ወደ አሜሪካ (ቦስተን) የላከውን ሻይ ቅጠል ባህር ውስጥ በመጨመር ቦስተን ቲ ፓርቲ ( Boston tea party) በመባል የሚታወቀውን ተግባር በማከናወን በእንግሊዝ ፓርላሜንት ውስጥ ውክልና ሳይኖረን ቀረጥ አንከፍልም(No taxation without representation) ብለው ታግለዋል:: ከዚሁ ከአሜሪካ ሳንወጣ ጥቁሮች ለእኩልነት ከታገሉበት እንድ ዋና መሣሪያና ሮዛ ፓርክንና በሁዋላም ማርቲን ሉተር ኪንግን ዝነኛ ያደረገው የሞንቶ ጎመሪው በስቦይኮት (bus boycott) ጥቁሮች ለእኩልነትና ለነፃነት የነበራቸውን ጥማት ያቀጣጠሉበት ዋና የትግል መሣሪያቸው እንደነበረ በታሪክ ይጠቀሳል::

የኢኮኖሚ ቦይኮትን በህንድ አገርም ሆነ በደቡብ አፍሪቃ ፀረ ቅኝ ግዛትንና አፓርታይድን እንደ መታገያ ዘዴ በመጠቀም ነፃነታቸውን እስከሚያገኙ ድረስ ተጠቅመውበታል:: ቦይኮትን በመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሙበትና ቃሉም ከጥቅም ላይ እንድውል ያደረጉት በአየርላንድ (Ireland) የሚኖሩ ጭሰኞች እንደነበሩ ይነገራል::

ታሪኩ እንደዚ ነበር:: የቃሉ ባለቤት የነበረው ሰው ቦይኮት( Captain Charles Cunningham Boycott) የአንድ በቦታው የማይኖር የመሬት ከበርቴ (absentee English landlord) ወኪል ሆኖ በሚሠራበት ጊዜ ጭሰኞቹ የሚከፍሉትን የመሬት ኪራይ እንድቀንስላቸው ይጠይቁታል፡ ቦይኮት ግን ቅናሽ ከማድረግ ይልቅ ይባስ ብሎ ገበሬዎቹን (ጭሰኞቹን) ከይዞታቸው እንድነቀሉ አደረጋቸው:: በዚህ ድርጊቱ የተበሳጩትና የተጎዱት ገበሬዎች ከካፒቴይን ቦይኮት ጋራ ምንም ዓይነት ግንኙነት ላለማድረግ ወሰኑ።

ማንም ሰው ለርሱ እንዳይሠራ፡ ማንም ሱቅ ያለው ሰው ለቦይኮት ምንም ነገር እንዳይሸጥለት፡ ፓሰተኞችም የፖስታ አገልግሎት እንዳያደርጉ ባጠቃላይ በማንኛውም ነገር ከካፒቴይ ቦይኮት ጋራ የሚደረግ ግንኙነት እንድቋረጥ በመደረጉና ቦይኮትም ይኸንን መቋቋም ስላልቻለ በአጭር ጊዜ ውስጥ አይርላንድን ለቆ ወዴ መጣበት ወደ እንግላንድ እንድመለስ ተገዶ ነበር::

ከላይ እንደተጠቀሰው ቦይኮትን በመጠቀም የተለያዩ አገሮች ከኢኮኖሚም ሆነ ከፖለቲካ ጭቆና ነፃ ወጥተዋል:: ቦይኮት ለሚለው ቃል አጠቃቀም ባለቤት የነበረውና የመሬት ከበርቴ ወኪል በመሆን ህዝብ ሲበድል የነበረውን ካፒቴይ ቦይኮትን ቦይኮት በማድረግ የአይረላንድ ጭቁን ገበሬዎች ድል እንደተቀዳጁ ሁሉ እኛም ኢትዮጵያውያን ፀረ-ህዝብ፡ ፀረ አንድነትና ፀረ ኢትዮጵያ የሆነውን ወያኔን በማንኛውም መንገድ(በኢኮኖሚ፤ በፖለቲካ፤ በማህበራዊ ኑሮ ወዘተ) ቦይኮት በማድረግ ወይንም ከህዝብ እንድገለልና ብቻውን እንድቆም በማድረግ ከእኩይ ዓላማው እንድታቀብና ከህዝብ የነጠቀውን ሥልጣን ለሥልጣን ባለቤት ለሆነው ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዳስረክብ ማስገደድ እንችላለን::

ሆኖም ግን ወያኔ ከካፒቴይን ቦይኮት ሚሊዎን ጊዜ የከፋ በደል በኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመ ወንጀለኛ ድርጅት ስለሆነ ሥልጣኑን በሰላም ለመልቀቅ አሻፈረኝ ካለና የሚሸነፈው ግደታ በህዝባዊ አመፅ ከሆነ እንደፈለገው መንገዱ ቀና ሆኖለት ወደ መጣበት ወደ ደደቢት ተመልሼ በሰላም እኖራለሁ ብሎ የሚያስብ አይመስለንም:: ምክንያቱም ነፃ እናወጣሃለን ተብሎ ቃል የተገባለት በተግባር ግን በስሙ የተነገደበትና ለወያኔ ግፍ አገዛዝ የመጀመሪያ ሰለባ የሆነው የትገራይ ህዝብ ስለሆነ ወንጀለኛችም ቢሆኑ የኛው ልጆች ናቸው ብሎ ለወያኔ አስቦ ለፍርድ እንዳይቀርቡ ይከላከልላቸዋል ብለን አናምንም:: ስለሆነም ወያኔዎች ዛሬ ቀን ሰጠን ብለው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ መቀለዳቸውንና ግፍ መሥራታቸውን በማቆም ከነርሱ በፊት የነበሩት አገዛዞች የደረሰባቸው ውድቀትና ውርደት ሳይደርስባቸው በጡንቻ የነጠቁትን ህዝባዊ ሥልጣን በፈቀዳቸው እንዳስረክቡ እንጣይቃለን::

 ድል ለኢትዮጰያ ህዝብ

ኢትዮጵያ በቆራጥ ልጆቿ መስዋትነት ነፃነቷ ተጠብቆ ለዘላለም ትኖራለች::

 

Ethiopia food inflation rate reaches over 100 percent  

African Press Agency (APA), March 12, 2009


APA-Addis Ababa (Ethiopia) The inflation of food prices in Ethiopia in January-February reached 104.1% up from 96 % in December 2008, Ethiopian Central Statistics Authority said in its latest report released on Thursday.

The report said inflation of food prices in the past six months increased by over 60%. The price of grains in July 2008 witnessed 52.2 % price inflation and 104.1 % in  January-February 2009, the report said.

The price inflation of non-food items, which was 11 % in the first six months of the Ethiopian new year, reached 22 % in September-February.

The report said the prices of food and non-food items are still on the rise despite the government efforts to control inflation.

Household items, liquor, various cosmetics, medical services and cigarettes are some of the non-food items that have shown a big price increase in the past few years.

Ethiopia is currently facing a foreign currency shortage due to the imbalance of its export and import trade. This has been resulted in high prices of imported items.


Enter supporting content here

Copyright 2004 Network of Ethiopian Women (NEW) International